The Soda Pop
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

☀:♥ለውጥን ያለ ስራ ማሰብ ቂልነት ነው።♥.☀:.


Ω እውነት መኖር ማለት መተንፈስ ብቻ ነውን?

Ω ሰርተን ራሳችነን ማስተዳደር ስንችል ሌሎች ሰርተው እንዲያስተዳድሩን እንሻለን?

Ω ጤናችንን መጠበቅ ስንችል ሌሎች ጤናችንን እንዲጠብቁልን እንፈልጋለን?

Ω እራሳችን ማንበብ ስንችል ሌሎች እንዲያነቡልን እንሻለን?

Ω በእውቀት የበለፀገ ፣ እራሱን በጥበብ የካነ ፣ ጤናማ ህይወትን መምራት የቻለ ፣ በዲናችን ጠንካራና የአሏህ ባሪያ መሆን ስንችል ፣ ኢስላማዊ ፅኑ የቤተሰብ ፍቅርን መስርተን መኖር ስንችል ፣ ማህባራዊ ኑሯዋችንና ፣ ስብዕናችነን ገርተን መኖር የምንችል ሆነን ያለ ጊዜያችነን ባረባ ነገር ማባከናችን ከንቱነት አይደለምን?

ሁሉም ሰው በሂወት ዘመኑ መለወጥና የለውጡን ነፀብራቅ ማየት ይሻል። ይህም ማለት በፊት ከነበረበት ሁኔታ በእውቀቱ ፣ በጤናው ፣ በኢማኑ ፣ በትዳሩ ፣ በማህበራዊ ኑሮው ፣ በስብዕናውና በስራ ልምዱ ለውጥን ማየት ይሻል። ይህን የምንሻው ለውጥ ግን ዝም ብለን እየተነፈስንና ያገኘነውን እየተመገብን በመኖር ብቻ የሚገኝ አይደለም። ይህን ለውጥ ለማግኘት መንቀሳቀስ መጀመርና ስራዎቻችነን በትጋት እንዲሁም በእቅድ መስራት ይኖርብናል።

ለውጥን ያለ ስራ ማሰብ ቂልነት ነው። ለውጥን ለማምጣትና ፍሬዋንም ለመቅመስ ግቦችን ቀርፀን ስራዎቻችነን በታታሪነት መስራት ይጠበቅብናል። ስራ መስራት በራሱ በቂ አይደለም። ከመስራታችን ባለፈ በምንሰራው ስራ መደሰትና የምንሰራው ስራ በእኛ ላይ ሊንፀባረቅ ይገባል። ለምሳሌ:-

አንድ ሰው የነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ሲራን አነብቢያለሁ ቢል ይህ ሰው ማንበቡ ብቻ በራሱ በቂ አይደለም። ባነበበው ነገር ሊስራራና ያነበበው ነገር በሱ ላይ ሊንፀባረቅ ይገባል። አለበለዚያ ትምህርት ቤት የገባሁሉ የተማረ ነው ብለን መደምደም ይሆንብናል።

ነገር ግን እውነታው ትምህርት ቤት መግባት አንድን ሰው አዋቂ ወይም የተማረ አያስብለውም። በእያንዳንዱ የክፍል የደረጃ በቂውንና ተፈላጊውን እውቀት እስካልጨበጠና በሂወቱ ላይ ተግባራዊ እስካልተገበረ ድረስ።

አብዛሃኛዎቻችን ጊዜያችነን ባረባ ነገር እናሳልፋለን። የሚገርመው ነገር ቢኖር መለወጥ እንፈልጋለን እንላለን። ህልምና ራዕያችነን ሁልጊዜም እንዘክራለን። ነገር ግን ለሰነቅነው ራዕይ እየሰራን አለመሆናችን በእያንዳችን ልብ ውስጥ ያለ እውነታ ነው።

ዛሬ ላይ ነገራቶችን መስራት ስንችል ነገ እሰራዋለሁ በማለት እራሳችነን እናታልላለን።

ΞΩ እስኪ በዲኑ ጠንካራ ፣
አዋቂ ለመሆን የማይፈልግ ማን ይኖር ይሆን? ጤናማና ፅኑ የቤተሰብ ፍቅርን መስርቶ መኖርን የማይሻ ማን ይሆን?

ΞΩ በዲኑ ጠንካራ ሆኖ ፣ አሏህን በቅን መንፈስ ተገዝቶ ፣ ጀነት መግባትን የማይሻ ማን ይኖር ይሆን?

ከላይ ለተጠየቁት ጥያቄዎች መልሱ ሁላችነም እንፈልጋለን ወይም የማይፈልግ ሰው የለም ነው ሊሆን የሚችለው። ከዚህ ውጭ መልስ ያለው ሰው የሚኖር አይመስለኝም። እዚህ ላይ ሌላ ጥያቄ ላንሳ:-

۵ ምን ያህሎቻችነን እውቀትን ለመሻት የምንሽቀዳደም?

۵ ሰዓታችነን በአግባቡ የምንጠቀምስ ስንቶቻችን እንሆን?

እስኪ በቀን ምን ያህል ጠቃሚና ራዕያችነን ከዳር ለማድረስ የሚጠቅሙንን ስራዎች በቀን ለምን ያህል ጊዜ እንደምንሰራቸው እንመልከትና አብዛሃኛውን ጊዜያችንን ከምናሳልፍበት ጊዜ ጋር እናነፃፅረው።

☀አስበን እንነሳ የለውጥ ቁልፍ በእጃችን ነው።☀


534

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ